Jump to content

አማር-ሲን

ከውክፔዲያ
የሐውልት ቅርጽ ያለው የሕንፃ መሠረት ችንክር፤ ንጉሥ አማር-ሲን እራሱ የህንጻ አሠሪ ዕቃ ሲሸከም ያሳያል።

አማር-ሲን ከ1918 እስከ 1909 ዓክልበ. ግድም ድረስ የኡርና የሱመር ንጉሥ ነበር። የአባቱ የሹልጊ ተከታይ ነበር። ቀድሞ ስሙ እንደ ቡር-ሲን በሊቃውንቱ ይታነብ ነበር፤ አሁን ግን አጠራሩ «አማር-ሲን» ትክክል እንደ ሆነ ይታመናል።

ለ፱ኝ ዓመቶቹ ሁላቸው በስም ይታወቃሉ። ዘመቻዎች በኡርቢሉምና በተለያዩ ቦታዎች (ሻሽሩም፣ ሹሩድሁም፣ ቢቱም-ራቢዩም፣ ጃብሩና ሑሕኑሪ) ላይ ይመዘገባሉ።[1] በተረፈ አማር-ሲን በኤላማዊ ነገሥታት እንደ ማርሐሺ ንጉሥ አርዊሉክፒ እንደ ዘመተ ይታወቃል። የዑር መንግሥት በአማር-ሲን ዘመን እስከ ስሜናዊ ግዛቶች እስከ ሉሉቢሐማዚ ድረስ ተዘረጋ። ደግሞ ዓመጽ በአሹር አሸንፎ አካዳዊ ሻካናካ (ከንቲባ) ዛሪቁምአሦር ላይ ሾመ።[2]

አማር-ሲን የሱመር ጥንታዊ ሥፍራዎች በተለይ በኤሪዱ የነበረውን ግንብ ለማሳደስ ሠራ።[3]

የባቢሎናዊ «ዋይድነር ዜና መዋዕል የተባለው ሰነድ እንዲህ ይላል፦ «የሹልጊ ልጅ አማር-ሲን የአኪቱ በዓል በሬና በጎች መሥዋዕት ቀየረ። በበሬ ውግያ እንዲሞት ተነበየ፤ ሆኖም ከጫማው መንከስ [ጊንጥ?] ሞተ።»

የአማር-ሲን ልጅ (ወይም ወንድም?) ሹ-ሲን በዑር ዙፋን ተከተለው።

ቀዳሚው
ሹልጊ
ሱመር ነጉሥ
1918-1909 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሹ-ሲን
  1. ^ Year-names for Amar-Sin
  2. ^ Potts, The Archaeology of Elam, p. 132.
  3. ^ Karen Frieden
pFad - Phonifier reborn

Pfad - The Proxy pFad of © 2024 Garber Painting. All rights reserved.

Note: This service is not intended for secure transactions such as banking, social media, email, or purchasing. Use at your own risk. We assume no liability whatsoever for broken pages.


Alternative Proxies:

Alternative Proxy

pFad Proxy

pFad v3 Proxy

pFad v4 Proxy