Jump to content

አና ፍራንክ

ከውክፔዲያ
Anne Frank (1941)

አና ፍራንክ ጀርመን በምትገኘው ፍራንክፈርት ከተማ ተወልዳ ያደገች፣በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ በሆላንድ ዋና ከተማ አምስተርዳም ትኖር የነበረች አይሁዳዊት ልጅ ነች። አና ከአባቷ ኦቶ ፍራንክ እና ከእናቷ አዲት ፍራንክ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1929 ዓ/ም ተወለደች።አባቷ ኦቶ ፍራንክ ትምህርት ወዳድ የቢዝነስ ሰው ነበሩ።የናዚ ጀርመን መንግስት ሆላንድን በወረራ ከተቆጣጠረ በሗላ ፣በግዛቱ ያሉ አይሁዳዊያንን እያሳደደ በማሰበር እና በማገት ወደ ለይቶ ማቆያ ካምፖች መላኩን አጠናክሮ ቀጠለ።እንደ አውሮጳዊያንን አቆጣጠር በ1942 የአና ፍራንክ ቤተሰቦችም ወደ ለይቶ ማቆያ ካምፖች እንዲላኩ ትእዛዝ ወጣባቸው።በዚህ ወቅት ሙሉ ቤተሰቧ ወደ ሲዊዘርላንድ ሸሽተው ከምድር በታች በሚገኝ መደበቂያ ቦታ መኖር ጀመሩ። በ1944 ዓ/ም ቤተሰቦቿ በተደረገባቸው ጥቆማዎች በናዚ ወታደሮች ተይዘው ለእስር ተዳረጉ።አና ፍራንክም የናዚ እስረኛ በመሆን በደረሰባት ግፍና መከራ በእስር ቤቱ የተነሳን ወረርሽኝ በሽታ መቋቋም አቅቷት በ15 አመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ሆኖም ግን ባለፉት አመቷ የጻፈቻቸው የግል ማስታወሻወች ዓለም አቀፍ ታዋቂነትን አትርፎላታል።


pFad - Phonifier reborn

Pfad - The Proxy pFad of © 2024 Garber Painting. All rights reserved.

Note: This service is not intended for secure transactions such as banking, social media, email, or purchasing. Use at your own risk. We assume no liability whatsoever for broken pages.


Alternative Proxies:

Alternative Proxy

pFad Proxy

pFad v3 Proxy

pFad v4 Proxy