«የ1812 መቅድም»
Appearance
维=>ሐ | ይህ መጣጥፍ «የሳምንቱ ትርጉም» ነው። (መጋቢት 4 ቀን 1998 ተመረጠ።) ችሎታ ካለዎት፣ ከሌሎቹ ቋንቋዎች መረጃ በትርጉም እንዲጨመር ይርዱ! |
«የ1812 መቅድም» ለኦፔራ ጓድ በፕዮትር ኢልዪች ቻይኮቭስኪ የተጻፈ ሙዚቃ ነው። ፈረንሳዮች በ1804 ዓ.ም. (1812 እ.ኤ.አ.) ወደ ሩሲያ በወረሩበት ወቅት የናፖሊዎን ሠራዊት ድል ስለሆነ ሙዚቃው ለጦርነቱ መታሠቢያ እንዲሆን ተጻፈ። ሙዚቃው በተለይ የሚታወቅበት የመድፍ ትኩስ ቅድም ተከተል በውስጡ ሊሰማ ስለሚችል ነው። አንዳንዴም የሙዚቃ ጓድ ሲያጫውተው በዕውነተኛ መድፍ ነው የሚደረገው። ምንም እንኳን በ1804 (1812) በአሜሪካ እና በእንግሊዝ መካከል ስለ ተዋገው ጦርነት ሙዚቃው አንዳችም ግንኙነት ባይኖረውም፣ በዩናይትድ ስቴት ውስጥ ብዙ ጊዜ እንደ አርበኞች ሙዚቃ ተቆጥሮ ይሰማል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |