አንድ
Appearance
አንድ በተራ አቆጣጠር መጀመርያው ቁጥር ነው።
ምልክቱ ከግዕዝ እንደ ትወረሰ ፩ ነው፣ ይህም ከግሪክ አልፋቤት መጀመርያው ፊደል አልፋ (በትንሹ «α») እንደ ተወሰደ ይታመናል። ኣንዳንድ ደራስያን ኣኃዞቹን ግሪኮች ቀዱ እንጂ ኢትዮጵያውያን ከግሪክ ኣልቀዱም ይላሉ። [1]
በብዙ ልሳናት የሚገኘው ምልክት 1 ከሕንዳዊ ቁጥር ምልክቶች ተደረጀ። እነዚህ ምልክቶች በአውሮፓ ከ968 እና 1550 ዓም መካከል እየተደረጁ ተቀባይነት አገኙ። ከዚያ አስቀድሞ በሮማውያን ቁጥር ምልክቶች የ«አንድ» ምልክት ፊደሉ «I» ነበር።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |